በድጋሚ የወጣ

የቢሮ ሕንጻ እና የሪከቨሪ መጋዘን ግዢ ጨረታ

ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ ለዋና መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ እና የተጎዱ ንብረቶችን ማቆያ/ሪከቨሪ መጋዘን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች በተመለከቱት አካባቢዎች፡- ማለትም

1. ለዋና መስሪያ ቤት የሚፈለግ ህንፃ

1.1 አካባቢ (Area) ፡-ከለገሀር – ቂርቆስ – ቄራ – ጎፋ መንገድ፤ ከጐተራ – ወሎ ሰፈር መንገድ፣ ከጐተራ /አጐና መስቀል ፍላወር – ኦሎምፒያ ፤ቸርችል ጐዳና ፤ ኡራኤል፤ ካዛንቺስ፣ከቡልጋሪያ ማዞሪያ (ቄራ)/ በበቅሎ ቤት  መስቀል ፍላወር ባለው አዲስ መንገድ ግራና ቀኝ አካባቢ ቢሆኑ ይመረጣል፣

2. ለሪከቨሪ መጋዘን የሚፈለግ ቦታ/መሬት

2.1 አካባቢ/Area/ ፡-ከቀለበት መንገድ አጠገብ እና/ወይም ውጭ ሆኖ አዲስ አበባ ከተማ በስተደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ ቢሆን ይመረጣል፡ ማለትም፡-ቃሊቲ – አቃቂ መንገድ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ለቡ፣ ሀና ማርያም እና በሌሎች ተቀራራቢ ቦታዎች ቢሆኑ ተመራጭ ነው፡፡

3. የጨረታ አቀራረብ

ለመሸጥ ፍላጐት ያላቸው ባለንብረቶች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ያለ ክፍያ በነጻ በቅሎ ቤት አካባቢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያው ዋ/መ/ቤት ሙጂብ ታወር ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ መጥተው በመውሰድ መጫረት ይችላሉ፡፡

3.1 ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት በወሰዱት የመጫረቻ ሰነድ ላይ ስለሚሸጡት ሕንጻ/ቦታ ዝርዝር ሁኔታውን በመሙላት የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡

3.2 ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ማለትም ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

3.3 ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ – በቅሎ ቤት የኢትየጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ አጠገብ ሙጂብ ታወር 1ኛ ፎቅ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-470-33-61 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

ሉሲ ኢንሹራንስ .